የጤና ሚኒስቴር የአመራር ክህሎት ሰልጣኞችን አስመረቀ

ግንቦት 3/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስቴር ለ3ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የአመራር ክህሎት ሰልጣኞችን አስመረቀ።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።
ሰልጣኞቹ በተለያዩ የአመራር አሰራር ክህሎት ላይ የሰለጠኑ ሲሆን ስልጠናው የአመራር ክህሎትን ለማጎልበት እና የሚኒስቴሩ አሰራር ለማጠናከር ያግዛል ተብሏል።
ተመራቂ ሰልጣኞች ስልጠናው በቤታቸው፣ በመስሪያ ቤታቸው እንዲሁም በጤናው አገልግሎት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በእመቤት ንጉሴ