“የጥላቻ ሰንሰለት” የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

ሚያዝያ 2/2014 (ዋልታ) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አየለ አዳቶ ዩማ የተጻፈ “የጥላቻ ሰንሰለት” የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ትውልድን ጥላቻን የማጣላት ዘመቻ ንቅናቄ 1ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ታስቧል።

መጽሐፉ ጥላቻን የሚገድለው የጥላቻ ጠላት ፍቅር እንደሆነ በሰፊው የሚዳስስ ነው ተብሏል፡፡

መጽሐፉ አሁን ያለው ትውልድ ከጥላቻ ተጣልቶ ይቅርታ፣ ሰላምና አንድነት ሰፍኖ ለማየትና ትውልድን ጥላቻ ማጣላትን ግብ አድርጎ እንደተነሳ ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ምክትል ኃላፊ አንተነህ ተስፋዬ ጥላቻን አጥልተን ስለፍቅር ከሰበክን ጥላቻን ማጥፋት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

በእመቤት ንጉሴ