የጨፌ ኦሮሚያ 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሀምሌ 9 ያካሂዳል

ሐምሌ 07/2013 (ዋልታ) – የጨፌ ኦሮሚያ 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሀምሌ ዘጠኝ እንደሚያካሂድ አስታወቀ::

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ በጉባኤው የመንግስት አካላት የስራ አፈፃፀም መገምገም፣ አቅጣጫዎችን መመልከት እንዲሁም ለ2014 በጀት አመት ለኦሮሚያ ክልል የፀደቀው በጀት እና አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ትኩረት ያልተቸረው ነገር ግን በግጭት አፈታት የረጅም አመታት እድሜ ያለውን የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን የመመስረት ረቂቅ በጨፌው ቀርቦ ውይይት ይደረግበታልም ተብሏል፡፡

ለ2014 በጀት አመት 124 ቢሊየን ብር መፅደቁን አስታውሰው፣ ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ29 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል::

በክልሉም በጨፌ አባላት የተከወኑ ስራዎች ምን ያህል ማህበረሰብ ተኮር ናቸው የሚለው የክትትልና የግብረ መልስ ስራዎች መሰራታቸው ተገልጿል::

በነገው እለትም የጨፌ ኦሮሚያ በሉሜ ወረዳ የችግኝ ተከላ መርኃግብር ያካሂዳል ተብሏል::

(በሄብሮን ዋልታው)