የፖሊስ አመራርና አባላት የእውቅና እና የምስጋና አሰጣጥ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

ግንቦት 28/2014 (ዋልታ) በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻዎች እንዲሁም በፖሊሳዊ ሥራዎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራርና አባላት የእውቅና እና የምስጋና አሰጣጥ መርኃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት ዋና ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ፣ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ተገኝተዋል።

“በመስዋትነታችን የሀገራችን አንድነት የሕዝባችን ሰላም ይረጋገጣል!” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለውን መርኃ ግብር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየታደሙ ነው።

በሜሮን መስፍን