ዩኒቨርሲቲው ለ11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

የካቲት 22/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

አግባብነት ባላቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርመሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ አጥጋቢ በሆነ መልኩ በባለሙያ ተገመግሞ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ታይቶ እና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን የሙሉ ፕሮፌሰርነት መረጃ የተመለከተው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ለ11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማጽደቁን የዩኒቨርሲቲው መረጃ አመላክቷል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. ቁምላቸው የሺጥላ (ዶ/ር)
  2. ሽመልስ አሰፋ (ዶ/ር)
  3. መንግስቱ ለገሰ (ዶ/ር)
  4. ጉታ ዘነበ (ዶ/ር)
  5. ፋሲል አሰፋ (ዶ/ር)
  6. ጥልዬ ፈይሳ (ዶ/ር)
  7. ብሩክ ላምቢሶ (ዶ/ር)
  8. ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር)
  9. ዘበነ ክፍሌ (ዶ/ር)
  10. ተረፈ ደገፋ (ዶ/ር) እና
  11. ንጉሴ ደዬሳ (ዶ/ር)ን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚሰጣቸው ምሁራን በመማር ማስተማሩ፣ በጥናትና ምርምር፣ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ አገልግሎት እንዲሁም በማኅበረሰብ ዐቀፍና ሙያዊ አገልግሎት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሌጅስሌሽን መሰረት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ለተወጡ እና ለዓለም የዕውቀት ስርጸት መዳበር ስኬታማ አበርክቶ ላደረጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች መሆኑን አስታውቋል።