ደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮ/ር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኮ/ር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) ‘የደህንነት ስጋት ናቸው’ ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ከእስር በመፍታት የተጠረጠሩት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የከተማው ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዳንኤል እሸቴ ለፋብኮ እንደገለፁት የፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ያለ ኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ከማቆያ እንዲወጡ አድርገዋል በሚል ነው።

በዚህ ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች አመራሮች መኖራቸውን በተመለከተም ከህዝብ ጥቆማዎች እየደረሳቸው እንደሚገኝ የገለጹት የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ መረጃውን ለማጥራት እየተሠራ ነውም ብለዋል፡፡