ዲያስፖራው ባለፉት 9 ወራት 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ልኳል

ግንቦት 9/2014 (ዋልታ) ዲያስፖራው ባለፉት 9 ወራት በሕጋዊ መንገድ 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ቤት መላኩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አመለከቱ።

የዲያስፖራው አባላትን የንግድ፣ ቱሪዘምና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከማሳደግ አንጻር ባለፉት 9 ወራት 97 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ የዲያስፖራ አባላት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

እንደኢዜአ ዘገባ ዲያስፖራው ለኅዳሴ ግድቡ በስጦታና በልዩ ልዩ ድጋፍ መስጫ ተግባራት 122 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ መፈጸሙንም አስታውቀዋል።

ለመከላከያ ሠራዊት ዲያስፖራው 109 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ 32 ሚሊዮን ብር ደግሞ ለበጎ አድራጎት ተግባራት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።