ዴንማርክ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ኅዳር 13/2014 (ዋልታ) ዴንማርክ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች፡፡

ድጋፉ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል እንደሆነ በኢትዮጵያ ከዴንማርክ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እርዳታው በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ የሚደረገውን ጥረት ያግዛልም ነው የተባለው፡፡