ድኅረ ግጭት ላይ ያተኮረ የምሁራን የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

ታኅሣሥ 21/2014 (ዋልታ) “ድኅረ ግጭት ላይ የምትመጣው ኢትዮጵያ ምን መልክ ሊኖራት ይገባል” በሚል መሪ ሐሳብ ላይ ትኩረት ያደረገ የምሁራን የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ በአገሪቱ የደረሰውን ውድመት መልሶ የማቋቋም ሥራ፣ ስነልቦናዊ፣ አካላዊና ማኅበራዊ ቀውስን እንዲሁም ፅንፍ የያዙ የምዕራባዊያንን ያልተገባ ጫና ተቋቁመን እንዴት መቆም እንችላለን በሚሉ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡

በመድረኩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት እየተሳተፉ ነው።

በድልአብ ለማ