ዶ/ር አሮሪት መሐመድ ከኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል መምሪያ ኃላፊ ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 29/2013 (ዋልታ) – በኡማን ሱልጣኔት የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር አሮሪት ሞሃመድ ያሲን በኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮሎች መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ካሊድ ቢን ሰይድ አል ጃራዲ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበረ ታውቋል፡፡

በውይይታቸውም በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን የድንበር ውዝግብ ፣ በአፍሪካ ህብረት የተመራውን የታላቁን ህዳሴ ግድብ የድርድር ሂደት ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡