ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆኑ

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) – ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላም ፈጽመዋል፡፡

አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር የክልሉን ትምህርት ቢሮ በኃላፊነት ሲመሩ የነበሩ ናቸው።

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ መስራች ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን፣ በጉባኤው ፋንቱ ተስፋየ  የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፤ አማረ ሰጤን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ መሰየሙ ይታወቃል፡፡