ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክኒያት ለተጎዱ የሰራዊት አባላት የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ

ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ

ኅዳር 13/2014 (ዋልታ) ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክኒያት ለተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚውል የህክምና መሳሪያዎች ለጤና ሚኒስቴር አስረከበ፡፡

ግሎባል አሊያንስ 15 ሚለየን ብር የሚያወጣ 300 የህክምና መሳሪያዎችን ለሚኒስቴሩ ያስረከበው።

ደርጅቱ ያበረከተው ኔጌቲቪ ዎንድ ቴራፒ የተሰኘው የህክምና ቴክኖሎጂ ሲሆን ቁስለኞች በቶሎ እንዲያገግሙ ይረዳል ተብሏል።

የግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታማኝ በየነ በውጭ የሚኖረው ዳያስፖራ እያደረገ ያለው ትብብርና ድጋፍ መቀጠሉን ተናግሯል።

በቀጣይም የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል።

 

በሚኪያስ ምትኩ