ግብርናን ማዘመን የላቀ ውጤት ያስገኛል – ጠ/ሚ ዐቢይ

መስከረም 6/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብርናን ማዘመን የላቀ ውጤት እንደሚያስገኝ ገለጹ፡፡

በጀመርነው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ክልል የዱግዳ እና የቦራ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻ መመልከታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፈረዋል፡፡

ክንውኑ እጅግ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን በመጠቆም የምሥራቅ ሸዋ ዞን ብቻ እንኳ 7 ሚልየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልጸዋል፡፡