ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለኅልውና ዘመቻ ድጋፍ

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ ) – የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ለኅልውና ዘመቻ የሚውል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አሥራት ዓፀደወይን (ዶ/ር) ተቋሙ በ2013 ከመማር ማስተማሩ በተጓዳኝ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ መልካምና አበረታች ሥራዎች ከውኗል ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸው የሆነውን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውም አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
ሰራተኞቹ ድጋፉን ያደረጉት “ከኅልውና የሚቀድም የለም” በሚል መንፈስ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ከዚህ ቀደም በነበረው የሕግ ማስከበር ወቅትም ከ4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡