ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በድርቅ ምክንያት የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ  መደገፍ እንደሚገባ ገለፁ

                                             ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጥር 26/2014 (ዋልታ) በድርቅ  ምክንያት የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ  መደገፍ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድርቅ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት በኦሮሚያ ክልል ቦረና  ዞን ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በማኅበራዊ ትስስር ገጻችው እዳስታወቁት በድርቅ  ምክንያት የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ  መደገፍ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ከከባድ ድርቅ ጋር በሚታገልበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ኦሮሚያ ክልል የቦረና ዞን ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጡን መፋለም አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በተለይም የመካከለኛ ጊዜ የውኃ ልማት ፕሮጀክቶች  መሰል ችግሮች ሳይከሠቱ መፍትሔ ለማበጀት እንደሚያስችሉም አመልክተዋል፡፡