ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከዓለም ዐቀፍ የገንዘብ ፈንድ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዓለም ዐቀፍ የገንዘብ ፈንድ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር ያላትን ትብብር ስለምታጠናክርበት መንገዶች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የለውጡን ሂደት በቀጣይነት ስለመደገፍ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።