ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት እንደሚያድግ ገለጹ

ግንቦት 30/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት እንደሚያድግ ገለጹ፡፡

በሕንድ በተካሄደው ምርጫ ናሬንድራ ሞዲ ለሦስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላስተላለፉላቸው መልዕክት አመስግነዋል፡፡

አጋር እንደመሆናችን መጠን ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት ያድጋል ሲሉም አክለዋል፡፡