ጠ/ሚ ዐቢይ ለፕሬዝዳንት ማክሮን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጠ/ሚ ዐቢይ

ሚያዝያ 17/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፈረንሣይ ፕሬዝዳንትነት ለሁለተኛ ጊዜ ተወዳድረው ለተመረጡት ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ጓደኛዬ ኢማኑኤል ማክሮን በታሪካዊ ምርጫ ዳግም በመመረጥህ እንኳን ደስ አለህ ብለዋል።

የሁለትዮሽ ግንኙነታችን የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸው አክለዋል።

ፕሬዝዳንት ማክሮን

ፕሬዝዳንት ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በመሆን ተቀናቃኛቸውን ማሪን ሊ ፐን በ58.2 በመቶ ለ 41.8 በመቶ በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን ፍራንስ24 ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW