ጠ/ሚ ዐቢይ ልዩነቶች አንድ ሆነን ከመኖር እንደማያግዱን የአውራ አምባ ማኅበረሰብ ህያው ምስክር ነው አሉ

ሰኔ 21/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እምነት፣ ብሔርና የፖለቲካ አመለካከት አንድ ሆነን ከመኖር እንደማያግዱን የአውራ አምባ ማኅበረሰብ ህያው ምስክር ነው አሉ።

“የጾታ እኩልነት፣ የሕጻናትና የአካል ጉዳተኞች ማኅበራዊ ፍትሕ በተግባር ተፈትኖ ያየንበት ማኅበረሰብ ነው።” ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ሃምሳ ዓመት በእነዚህ ዕሴቶች ጸንቶ መኖር ድንቅ ብቻ ሳይሆን ተአምርም ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡