ጠ/ሚ ዐቢይ በምግብ ራስን ለመቻል እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ነው አሉ

መጋቢት 13/2014 (ዋልታ) በምግብ ራስን ለመቻል እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በምስራቅ ሸዋ አዳማ ወረዳ ወንጂ ኩሪፍቱ ቀበለ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርትን ጎብኝቷል።

ሁሉም ዜጋ ስለነፃነት ለማውራት የኢኮኖሚ ነፃነቱን ማረጋገጥ እንዳለበት የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ የሰጠውን ልዩ ትኩረት በተለይም ወጣቱ ትውልድ ትኩረት አድርጎ ለለውጥ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የዓለም ባንክ የአፍሪካ ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ታውፊላ ኒያማድ ዛቦ ኢትዮጵያ እያደረገች ላለው ጥረት ባንካቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ተናግረዋል።

በጉብኝቱ የዓለም ባንክ የአፍሪካ ተወካይ ዋና ዳይሬክተር፣ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ተወካይ ዳይሬክተር እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሚልኪያስ አዱኛ