ለአኅጉራዊ አንድነት ራዕይ መሳካት ቁርጠኛነታችንን እናረጋግጣለን – ጠ/ሚ ዐቢይ

የአፍሪካ ቀን

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) “በዘንድሮው የአፍሪካ ቀን ላይ ሆነን ለአኅጉራዊ አንድነት ራዕይ መሳካት ቁርጠኛነታችንን እናረጋግጣለን” ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የሚከበረውን የአፍሪካ ቀንን ምክንያት በማድረግ በቲውተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክታቸው “አያቶቻችን የነበራቸውን ሰላማዊ፣ የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካን እውን የማድረግ ራዕይን ለማሳካት ቁርጠኛ ነን” ብለዋል።

የአፍሪካ ቀን በአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ግንቦት 25 በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን ቀኑም የዛሬው የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሆኖ የተመሰረተበትን ቀን መሰረት በማድረግ መከበር የጀመረው።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW