ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከ2.3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የኢመደኤ ዋና መስሪያ ቤትን መረቁ

ሚያዝያ 09/2013 (ዋልታ) – ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና መስሪያ ቤት በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተመረቀ።

በ21 ሺህ 371 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ህንፃው 5 የተለያዩ ራሳቸውን የቻሉ ፎቆች እና 1 ባለ 2 ወለል የንግድ ማዕከልን የያዘ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 4 ባለ 14 ወለል ፎቆች እና 1 ባለ 17 ወለል ህንፃ ይገኝበታል፡፡

በህንፃው ኢመደኤ፣ ሰላም ሚኒስቴር፣ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ እና የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ይገለገሉበታል ተብሏል፡፡

ኢመደኤ የኢንፎርሜሽን የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚሠራ ተቋም እንደመሆኑ እንደዚህ አይነት ዘመናዊ የቢሮና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ህንፃ ከማስፈለጉም በላይ ተቋሙ በየዓመቱ ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣውን ከ87 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚያስቀር መሆኑ ተገልጿል፡፡

(በአስታርቃቸው ወልዴ)