ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከካናዳው አቻቸው ጋር ተወያዩ

 

የካቲት 18፣ 2013 (ዋልታ) – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በሀገራዊ እና ቀጣናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

ካናዳ ለኢትዮጵያ የዘወትር አጋር ሆና መቆየቷን አንስተው ባለፈው ግንኙነታችን ላይ ተመሥርተን ትብብራችንን እናጠናክራለን ሲሉ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ጠ/ሚ ዐቢይ በነበራቸው ገንቢ የውይይት ቆይታ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶን አመሰግነዋል፡፡