ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከ2010 ጀምሮ በፋይናንሱ ዘርፍ ስኬታማ ለውጦች መመዝገባቸውን ገለጹ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሚያዝያ 29/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ2010 ጀምሮ በፋይናንሱ ዘርፍ ስኬታማ ለውጦች መመዝገባቸውን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፋይናንስ ዘርፍ ዐበይት ስኬቶች በሚል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት የታክስ ገቢ በ2010 ከነበረበት 229 ቢሊየን ብር በ2012 የ36 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 311 ቢሊየን ማድረስ ተችሏል።