ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸለሙ

መስከረም 4/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሻሻል ባደረጉት ጥረት የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “እንደ ሀገር ዘርፉን አካታች ለማድረግ ስለ ተጓዝናቸው ምዕራፎች ይህንን ሽልማት በመቀበሌ ክብር ይሰማኛል” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ያካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገትና መሻሻል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነው ከዓለም አቀፉ ኢስላሚክ ፋይናንስ አመራር ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡