ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት በሆነው ኮቪድ-19 ዙሪያ መወያየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ እና ጀርመን መካከል ያለውን የልማትና የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡