ጠ/ሚ ዐቢይ ከጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መሪዎቹ በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያም ምክክር ያደረጉ ሲሆን፣ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነትን በጠበቀ መልኩ የሁለትዮሽና የቀጣናዊ ግንኙነትን ለማጠናከር መነጋገራቸውም ታውቋል።