ጠ/ሚ ዐቢይ ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በመጪው ምርጫ ዙሪያ ተወያዩ

 

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በ6 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ሲወያዩ

የካቲት 17/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በመጪው ግንቦት ስለሚካሄደው ምርጫ መወያየታቸውን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች እና ኃላፊነቶች አንድ ተደርገው እንዳይቆጠሩ ግልጽ መለያዎች መቀመጣቸውን ነው የገለጹት፡፡

በዚህ ምርጫ የመንግሥት ኃላፊነት ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው ብለዋል።

በዚሁ መሠረት፣ የክልል ብሔራዊ መንግሥታትም በምርጫው ሂደት ተወዳዳሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማገዝ ቁርጠኝነትን ማሳየታቸውንም ፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡