ጠ/ሚ ዐቢይ የበዓሉን ዋዜማ ከወልድያ ሕዝብና ሠራዊታችን ጋር በማክበሬ ደስታ ተሰምቶኛል አሉ

ሚያዚያ 22/2014 (ዋልታ) የዒድ አል ፈጥርን ዋዜማ ከወልድያ ከተማ ሕዝብና በአካባቢው ካለው ሠራዊታችን ጋር በማክበሬ ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ጀግናው ሠራዊታችን የሕዝቡን ደኅንነት እና ልማት በደሙ ለማስከበር ወትሮ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል” ብለዋል።
ይሄንን ሕዝብና ሠራዊት በዓላማ አንድነት ያጸናውን ግንብ እንኳን ሊደፍሩት ሊጠጉት አስፈሪ ነው ሲሉም አክለዋል።