ጠ/ሚ ዐቢይ የኢትዮጵያና ጅቡቲ ትሥሥር ታሪካዊ እና ጥልቅ መሠረት ያለው ነው አሉ

መጋቢት 19/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ያለው ትሥሥር ታሪካዊ እና ጥልቅ መሠረት ያለው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከጉርብትና ባለፈ ቤተሰባዊነት ያለው ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት “ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና እኔ ነባሩን መሠረት ለሀገሮቻችን የጋራ ብልጽግና መሸጋገሪያ ልናደርገው ቁርጠኞች ነን” ብለዋል፡፡

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!