ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዲያስፖራዎች ጥሪ አቀረቡ

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 1 ሚሊዮን ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያንና ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀላቀሉ ጠየቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገፃቸው የአውሮፓዊያኑን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር መንግሥት ያቀደውን 1 ሚሊዮን ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀላቀሉ ነው የጠየቁት፡፡