ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቻይና በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቻይናው የኢስተርን አየር መንገድ በረራ ቁጥር MU735 በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የተማሰቸውን ጥልቅ ሀዘን በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት እንዲሁም በራሳቸው ስም ለቻይና ሕዝብና መንግሥት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በላኩት ደብዳቤ በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች መጽናናትን እንደተመኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!