ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጣና ፎረም ለመሳተፍ ባህርዳር ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጥቅምት 5/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጣና ፎረም ለመሳተፍ ባህርዳር ገቡ።

ፎረሙ ከ2004 ዓም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የዘንድሮው የጣና ፎረም ”የደኅንነት ስጋቶችን በመቆጣጠር በአፍሪካ የማይበገር አቅም መገንባት” በሚል ይካሄዳል።

ፎረሙ ትናንት የቀድሞውን የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንዳን በማሰብ በቅድመ ጉባኤ ደረጃ መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል።

ዛሬ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የአፍሪካ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካላት በተገኙበት በይፋ የሚጀመር ሲሆን የአፍሪካ የሰላምና ደኅንነት ችግሮችን አፍሪካዊ በሆኑ የመፍትሔ አቅጣጫዎች መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ጣና ፎረም የአፍሪካ ህብረት እ.አ.አ በ2009 ለአፍሪካ ችግር አፍሪካ ተኮር መፍትሄ እንዲበጅ ያስቀመጠውን ”የትሪፖሊ ዲክላሬሽን” መሰረተ አድርጎ የተቋቋመ ፎረም ሲሆን የፎረሙ ዋነኛ ዓላማም አፍሪካን እየፈተነ ለሚገኘው የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ላይ የአኅጉሪቷ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪዎችና የዘርፉ ምሁራን በጋራ በመምከር አኅጉራዊ የሆኑ መፍትሔ እንዲያበጁ ምቹ መደላድል መፍጠር ነው።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW