ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መልካም ድል ተመኙ

መጋቢት 17/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የመልካም ድል ምኞታቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ብሔራዊ ቡድኑ በአሁኑ ወቅት “የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉን አስፍቷል“ በማለት ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ጫፍ መድረሱን አስታውሰዋል።
በዚህም “ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው ያስገኙት ድል ትልቅ አርአያነት አለው” ሲሉ የብሔራዊ ቡድኑን ስኬት አድንቀዋል።
“በቀጣዩ ጨዋታቸው መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ” በማለት የመልካም ድል ምኞታቸውን ገልጸዋል።