ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያዊያን የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻን እንዲቀለብሱ ጥሪ አቀረቡ

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኅዳር 8/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊያን ሀሰተኛ ትርክትን ለመቀልበስ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ፡፡

በኢትዮጵያ ላይ የሃሰተኛ መረጃ ጦርነት መከፈቱን መዘንጋት እንደማይገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል፡፡

ጣላት አገር የማፍረስ አደገኛ መንገዱን በጦር ግንባር ብቻ ሳይሆን በሀሰተኛና የፈጠራ ወሬዎች ስርጭትም ዘመቻ እንደከፈተ በመጠቆም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስሁት ትርክቱን ባለመቀበል ለመቀልበስ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ነው በቲውተር መልዕክታቸው ያመለከቱት፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፣  በሩቅ እና ቅርብ ያሉ፣ የአገራችንን በጎ የማይፈልጉ አካላት ያለ የሌለ ሀብትና ጉልበታቸውን ተጠቅመው፣ በአገራችን ላይ የተበላሸ ትርክትን የመጫን ጦርነት መክፈታቸውን አንዘንጋ።  በብሔር ላይ እየተሰራ ያለውን የተዛባ ትርክት ለመቀልበስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሚና መጫወት አለበት።  በኅብረ ብሔራዊ አንድነት የራሳችንን ታሪክ እኛው እንሰራለን፤ እኛው እንጽፋለን!›› ሲሉ ነው የጻፉት፡፡