ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨትን አስጀመሩ

የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት

የካቲት 13/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ቁልፍ ተጭነው ኃይል ማመንጨት አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በጉባ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓባይ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችለውን ቁልፍ ተጭነው ዓባይ ለኢትዮጵያ ኃይል እንዲያመነጭ አድርገዋል።

ግድቡ ኃይል ማመንጨት የጀመረው ካሉት 13 ተርባይኖች በአንዱ ተርባይን አማካኝነት ሲሆን 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።