ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉባኤው በአኅጉራቱ መካከል ትብብርና አጋርነትን ለማጠናከር እንደሚያስችል እምነቴ ነው አሉ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ ኅብረት እና የአውሮፓ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በሁለቱ አኅጉራት መካከል ያሉትን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው እምነቴ ነው አሉ።

መድረኩ ወቅታዊ እና ቀጣይ የትብብር እና የአጋርነት ሥራዎች ለማጠናከርና ዘላቂ ለውጥን ለማምጣት የሚያስችል ግብዓት እንደሚያስገኝ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

ለዚህም ተፈጻሚነት ኢትዮጵያ እንደ ቀደምት የአፍሪካ ኅብረት መሥራችነቷ የበኩሏን ሚና እንደምትጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ባሰፈሩት መልእክት ጠቅሰዋል።

ጉባኤው በቤልጅየም ብራስልስ መካሄድ ጀምሯል።