ጡት በማጥባት 40 በመቶ የጨቅላ ህፃናት ህይወትን ከሞት መታደግ እንደሚቻል ተጠቆመ

ሐምሌ 27/2014 (ዋልታ) ጡት በማጥባት ብቻ 40 በመቶ የጨቅላ ህፃናት ህይወትን ከሞት መታደግ እንደሚቻል ተጠቆመ።

በኢትዮጵያ ለ14ኛ በዓለም ለ30ኛ ጊዜ የጡት ማጥባት ሳምንት ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 1 ቀን “ምቹ ሁኔታ ለሚያጠቡ እናቶች፣ እናስተምር፣ እንደግፍ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

በመጀመሪያዎቹ 1 ሺሕ ቀናት ውስጥ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት እንዳለባቸውና ጡት ማጥባት ደግሞ አንዱ የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ መሆኑ ተጠቁሟል።

የምግብና ሥርዓተ ምግብ ቡድን አስተባባሪ ህይወት ዳርሰኔ ጡት ማጥባት ለህፃናት ዓይነተኛ የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

ሳምንቱ የሚከበረው ለህፃናት፣ ለእናቶች፣ ለማኅበረሰቡ የጡት ማጥባት ጠቀሜታን በዘላቂነት ለማስተማር መሆኑንም ተናግረዋል።

በትዕግስት ዘላለም