ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ አንዳንድ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስለ ኢትዮጵያ የሚዘግቡበት ሁኔታ የተዛባ ነው አለች

ታኅሣሥ 19/2014 (ዋልታ) ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ ፍራንቼስካ ሮቺን አንዳንድ የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚዘግቡበት ሁኔታ የተዛባ እና ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን ገለጸች፡፡
ፍራንቼስካ ከኤፍቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢዎች ለአሸባሪው ሕወሓት ያደላ አዘጋገብ እንደሚከተሉ ጠቅሳ እንደ ጋዜጠኛ የሁለቱን ወገኖች ቃል ያካተተ እና በትክክል በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ የሚያሳይ ዘገባ መሥራት እንደነበረባቸው አንስታለች፡፡
ጋዜጠኛዋ ሲ ኤን ኤን አዲስ አበባ በሕወሓት ቁጥጥር ስር ልትወድቅ መሆኗን መዘገቡ ከሚስተዋለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የጣቢያውን ብሎም የምዕራባውያኑን መገናኛ ብዙኃን አድልዖ እና የሃሰት ዜና ያጋለጠ ሁነት እንደነበርም ነው ያመላከተቸው።
ምዕራባውያኑ ስለ ኢትዮጵያ የሚያወጡት መረጃ የተሳሳተ እና ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን ጠቁማ መንግሥት የሚሰጣቸውን መረጃ ከተባለው ዓውድ ውጪ አዛብተው በመተንተን ያቀርባሉ ብላለች፡፡
ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መረጃ ከመገናኛ ብዙኃን ሲሰጠው እንዳለ ከመቀበል ይልቅ እንዴት ብሎ መጠየቅ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት መፈለግ ተገቢ መሆኑን በአጽንኦት ተናግራለች፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!