ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አደረገች

ጥር 20/2014 (ዋልታ) ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ድጋፉን ኢትዮጵያ በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት በተያዘው ሳምንት መረከቧን በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ድጋፉ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ያገኘች ቀዳማ አገር ያደርጋታልም ነው የተባለው፡፡

ይህ አቅርቦት ከዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ግሪክ፣ ጣሊያንና ስዊድን ጋር በዩኒሴፍ ድጋፍ 13 ሚሊዮን የክትባቶች ዓለም ዐቀፍ ልገሳ አካል መሆኑም ተገልጿል፡፡