ፈረንሳይ ለፖላንድ ሁለት የምልከታ ሳተላይቶችን ለመሸጥ ተስማማች

ታኅሣሥ 19/2015 (ዋልታ) ፈረንሳይ ለፖላንድ ሁለት የምልከታ ሳተላይቶችን ለመሸጥ መስማማቷ ተገለጸ፡፡

በዚህም ሳተላይቶቹን ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውን የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስትር ሰባስቲያን ሉኮርኙ በቲዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል፡፡

የፖላንድ ጦር መሳሪያ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በስምምነቱ መሰረት ፖላንድ 575 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ በማውጣት ሁለቱን ሳታላይቶች ትቀበላለች፡፡

የኤር ባስ መከላከያና ስፔስ ምርት የሆኑት ሁለቱ ሳተላይቶች ለፖላንድ የህዋ አገልግሎት እንዲውሉ የተከላ ስራዎች በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2027 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡