“ፊቼ ጫምባላላ” በዓል በሀዋሳ ከተማ ዛሬ መከበር ይጀምራል

“ፊቼ ጫምባላላ” በዓል
 
ሚያዝያ 20/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” በሀዋሳ ከተማ ጉዱማሌ በደማቅ ሁኔታ ዛሬ መከበር ይጀምራል።
 
በአደባባይ በሚከበረው የሲዳማ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል ላይ የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች እንግዶችም ይታደማሉ ተብሏል።
 
ከሚያዝያ 20 እስከ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በሲምፖዚየምና ሌሎች ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
 
የሰው ልጆች ወካይ የዓለም ቅርስ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” አብሮነትን፣ ሰላም፣ መረዳዳትን በሚያጠናክሩ መሰናዶዎች ለማሳለፍ እንደታሰበም ከወጣው መርኃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
 
በየዓመቱ የሚከበረው የሲዳማ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ከሀዋሳ በመቀጠል በመዲናዋ አዲስ አበባ ለማክበር እንደታሰበ ተጠቁሟል።
 
የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ፍቼ ጨምባላላ” ከሰባት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ እና ባህል ድርጅት “ዩኔስኮ” ከማይዳሰሱ የሰው ልጆች ባህላዊ ሀብቶች ስር መመዝገቡ የሚታወስ ነው።
 
 
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!