ፌደሬሽኑ ከሥራ አስፈፃሚነት የታገዱት ሶፍያ አልማሙ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ወሰነ

ታኅሣሥ 24/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ሲጠናቀቅ ከሥራ አስፈፃሚነት የታገዱት ሶፍያ አልማሙ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ወሰነ፡፡
በዚህም ከዚህ ቀደም በተፈጠረው የአሰራር ክፍተት ምክንያት ከኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚነት ታግደው የቆዩት ሶፍያ አልማሙን ወደ ሥራ አስፈፃሚነት ቦታቸው እንዲመለሱ የውሳኔ ሐሳብ ለጉባኤተኛው ቀርቦ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
አበበ ገላጋይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።
በተጨማሪም ዮሴፍ ካሳ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው መጋቢት 2014 በአዲስ አበባ እንደሚደረግ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡