ፍርድ ቤቱ በበጀት ዓመቱ 176 ሺሕ 797 መዛግብት ላይ ውሳኔ ሰጠ

ነሐሴ 4/2014 (ዋልታ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2014 በጀት ዓመት 176 ሺሕ 797 መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠቱን ገለጸ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ በበጀት ዓመቱ የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍና ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው ገልፀዋል።

የቀረቡ ጉዳዮችን እንደየ ጉዳዩ ቅለትና ክብደት ቀልጣፋና ፈጣን ውሳኔ መስጠት ተችሏል ነው ያሉት።

የ2014 አፈፃፀም ከ2013 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ5ሺሕ 521 መዛግብት ብልጫ አለው ብለዋል።

በ391 ዳኞች አማካኝነት መዛግብቱ እልባት ያገኘ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን 451 ለአንድ ዳኛ እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡

በበጀት ዓመቱ የዳኞች ነፃነትን ለማረጋገጥና ዳኞች ሕግና ህሊናቸውን ተጠቅመው እንዲወስኑ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።

በዳኞች ላይ ይነሱ የነበሩ እንደ ሙስና ያሉ የስነ ምግባር ችግሮች ላይ አስተማሪ እርምጃ ተወስዷልም ብለዋል።

በትዕግስት ዘላለም