ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከዓለም ዐቀፉ የማላመድ ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

ሐምሌ 7/2014 (ዋልታ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከዓአለም ዐቀፉ የማላመድ ማዕከል (ጂሲኤ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓተሪክ ቨርኩጅን (ፕ/ር) ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የማላመድ እቅድ አዘጋጅታ እየተገበረች መሆኗን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እንደ አገር እና አፍሪካ እንደ አህጉር ለአየር ንብረት ለውጥ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ቢሆንም በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርስባቸው ተፅዕኖ ግን ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዓለም ዐቀፉ የማላመድ ማዕከልእና የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ መላመድ የማፋጠን ፕሮግራም ለመደገፍ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሰባሰብ እየሰራ እንደሆነ ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የተግኘው መረጃ ያሳያል፡፡