ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለኤርትራ የነፃነት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኤርትራ የነፃነት ቀንን አስመልክተው ለአገሪቱ መንግሥት እና ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የኤርትራ የነፃነት ቀንን አስመልክተው በኢትዮጵያ ለኤርትራ ኤምባሲ በላኩት ደብዳቤ ለኤርትራ መንግሥት እና ሕዝብ ሰላም እና ብልፅግና እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡
በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኤርትራን የነፃነት ቀን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ወንድማማች የሆኑት ሁለቱ አገራት ያላቸው ትብብር የአገራቱን እድገት እንደሚያፋጥን እና ሕዝቦቹንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ መረጃ እንሚያሳየው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ለኤርትራ መንግሥት እና ሕዝብ ሰላም፣ ፍቅር እና ስኬትን ተመኝተዋል፡፡