ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ተሳታፊዎች አትሌቶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ነሃሴ 6/2013(ዋልታ) – የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ   መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አገራችንን በመወከል በየዉድድሩ ዘርፍ ተወዳድረው  የአቅማቸዉን በመፈጸም ወርቅን ጨምሮ ሜዳሊያ ላስገኙ፡ በአጠቃላይ ለተወዳደሩት አትሌቶች በሙሉ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ  የአትሌቶቹ የልምምድ ሥፍራ ላይ በመገኝት በመጨረሻም በቤተ መንግሥት ሽኝት በማድረግ እንዳበረታቷቸዉ፡ መንግሥትም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በመመደብ አትሌቶችን ለመደገፍና ለማብቃት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን አስታውሰዋል ፡፡

ፕሬዝዳንቷ እንዳሉት እንደ አሸኛኘቱ ሁሉ በቀጣይ  ይፋዊ  አቀባበል የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን  ተሳትፎ በተመለከተ ፕሬዚደንቷ ዝርዝር ሪፖርት እንደሚጠበቁም  ማስታወቃቸውን  ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡