ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ማረፍ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ማረፍ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዝዳንቷ “ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ አምላካቸው ሄደዋል፤ ልባዊ ሃዘኔን ለቤተሰባቸውና ለመላ ኢትዮጵያዊያን እገልጻለሁ” ሲሉ ነው የሀዘን መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

“ትላንት ሆስፒታል ስለነበርኩ ስለ ጤንነታቸው የሰማሁት አሳስቦኝ ነበር” ያሉት ፕሬዝዳንቷ “ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን፤ በክብር እንሸኛቸው” ሲሉም አክለዋል::

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW