ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እስልምና እምነት ተከታዮች ድጋፍ አደረጉ

ግንቦት 02/2013 (ዋልታ) – ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ በዓልን ለማክበር የሚያግዝ ድጋፍ አድርገዋል።

ፕሬዝዳንቷ በዚህ ሳምንት የሚከበረውን የኢድ በዓል ለማክበር የሚያግዙ የተለያዩ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፎችን  ነው ያደረጉት።

ድጋፉን ያበረከቱት በዛሬው ዕለት በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስ ፕሬዝዳንቷ ላበረከቱት ድጋፍ አመስግነዋል።

ፕሬዝዳንቷ የተቸገሩ ወገኖችን ለማገዝ ያደረጉት ድጋፍ አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸው፣ ሌሎችም ይህንኑ ፈለግ በመከተል ሰብዓዊነታቸውን እንዲያሳዩ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ባለፈው ዓመት በረመዳን መሳለሚያ እህል በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመገኘት ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።