ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ኢትዮጵያ ከየሀገራቱ ጋር ያላትን የወዳጅነት ትብብር የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገለጹ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ኢትዮጵያ ከሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገለጹ

መጋቢት 28/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ ከሀገራት ጋር ያላትን ወዳጅነትና ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት በአጽንኦት ገለጹ፡፡

ፕሬዝዳንቷ ይህንን ያሉት አዲስ የተሾሙ የአምስት አገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት ነው፡፡

የሹመት ደብዳቤ ያቀረቡትም ዙሀይር እንሶር የዮርዳኖስ አምባሳድር፣ ኮንራድ ቪንሴንት የሲሸልስ አምባሳደር፣ ማስ ኤንዮ የኮት ዲ ፎር አምባሳደር፣ ኤርቬ ዳድጀድጂ የቤኒን አምባሳደር እና ዳኒኤል ኦዋሳን የኮንጎ ሪፐፒሊክ አምባሳደር መሆናቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የቤኒን ኤምባሲ እ.አ.አ 2020 መጨረሻ ላይ ተዘግቶ እ.አ.አ 2021 መጨረሻ መከፈቱንም ጽሕፈት ቤቱ አስታውሷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW